ይህ “ዶቃ “የተሰኘው አማርኛ ፊልም የፓን አፍሪካን የፊልም ፌስቲቫል (Best Feature Film) ዘርፍ እና የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን አሸናፊ መሆን የቻለ ነው ተብሏል::
ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ፊልሙን ለማዘጋጀት ሦስት አመት እንደወሰደባት እና ጥሩ ነገር ለተመልካች አቅርበናል ብላ እንደምታምን ገልጻለች።
በፊልሙ የሃገራችን እንቁ ባለሙያዎች እንደ ቅድስት ይልማ፣ቤዛ ሃይሉ ፣ ማህደር አሰፋ እና ሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች እንደ ተሳተፉበት ታውቋል።
አቶ በሱፍቃድ ተመልካቾች ፊልሙን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት ይቻላል ያሉ ሲሆን፣ ለመመልከት መመዝገብ እና ከፍያ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል።
አቶ በሱፍቃድ ክፍያው ሁሉን ያገናዘበ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ውስጥ 100 ብር፣ለውጭ ደግሞ 5 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የቴሌ ቲቪ ከፍያን ለመፈፀም ለሃገር ውስጥ ቴሌብርን ፣ ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና አሜሪካን ኤከስፕረስን በመጠቀም መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል።
ኢግልላየን ፤ቴሌ ቲቪን ጨምሮ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ከመንግስት ተቋማት ፣ ከባንኮች እና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት በማበልጸግ ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡
የኢግልይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፍቃድ ፤ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ሰኔ 27 /2016 ዓ.ም “6 ሰዓት ከለሊቱ” እና “ትዝታ” የተሰኙ ሁለት የአማርኛ ፊልሞችን ይዞ መመረቁን አስታውስዋል::

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ