ረቡዕ 15 ጃንዋሪ 2025

ዳጉ

ዳጉ

ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡ ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ዳጉ ማለት በግርድፉ በአማርኛው ዜና ወይም በእንግሊዝኛ news/እንደ ማለት ነው፡፡ ዳጉ በተለያዩ የእድሜ ክልል የሚገኙ የተለያየጾታ ያላቸው አፋሮች በባህላዊው በታወቀ ስነ-ስረአት መሰረት አድርጎ የሚደረግ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡

 ዳጉ ማለት አንድን መረጃ ማዳመጥ መመልከት ብቻ ሳይሆን እንደሰማውና እንደአየው አድርጎ ለሌሎች ሲያስተላልፍ ባህላዊ ሀላፊነት /ግዴታ ጭምር የሚያቅፍ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

ዳጉ በዘመኑ ቴክኖሎጂ እይታ ከተመለከትነው ዳጉ ገመድ አልባ ፈጣን የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ምንም አይነት ቴክኖሎጂን ሳይጠቀሙ መረጃን በአጭር ጊዜ ወደ ብዙ ቦታ ለብዙ ሰዎች ደርሶ ተግባራዊ ምላሽ የሚደረግበት ባህላዊ

ዘመናዊ መረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ስለሆነም ካንድ ቦታ የተገኘዉ መረጃ በፍጥነት ፣ በጥራት - ሳይዛባ በቶሎ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

ዳጉ መጥፎውን ና ጥሩውን ማህበረሰቡ የሚለይበት ስርአት ነው፡፡ ዳጉ ልክ እንደ ምግብና ውሀ ነው፡፡ አፋሮች ሁሌ ይንቀሳቀሳሉ ትንሽም ብትሆን መረጃ እንድታመልጣቸው አይሹም፡፡ በጠቅላላ ዳጉ ማለት ስለ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ከአንድ ወደ ሌላ የሚተላለፍ መረጃ ነው፡፡ 



እሑድ 12 ጃንዋሪ 2025

ዳማ ከሴ

 ዳማ ከሴ 

በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን እንደ ከሴ (ስ. ጥሩ ሽታ ያለው የቁጥቋጦ አይነት። ዕቃ ማጠኛ ወይም ኮሰረት  ያለ ለመድኅኒትነት የሚጠቀሙበት ነው።

ይሄ ዕጽ በሺ ስድስት መቶ እስከ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሜትር ከፍታ ባሉ ሥፍራዎች የሚበቅል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመድኅኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሐ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።

የዳማ ከሴ ተጨማሪ ጥቅሞችለ

ጉንፋን፣ ለራስ ምታትና ለውሻ ልክፍት (በተለምዶ - ያድን አያድን አይታወቅም) ይጠቀማል።



ማክሰኞ 7 ጃንዋሪ 2025

ራያ

  ራያ

 በደቡብ ትግራይ እና በሰሜን ወሎ የሚገኝ ህዝብ  እና አካባቢ ነው። ይህ ህዝብ በትግራይ እና በወሎ ካሉ ደማቅ ባህሎች ባለ ቤት ስርዓት እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስርዐት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይም ሙስሊም  ክርስቲያን  ሳይል በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ "ጉማየ" "መጋልዋ" ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን ወጀራትና እንደርታ፣ በደቡብ የጁ (ጉባ ላፍቶ) እና ሃብሩ፣ በምስራቅ ዓፋር፣ በምዕራብ ደግሞ ግዳን እና ዋግኽምራ ያዋሱኑታል።




ዓርብ 3 ጃንዋሪ 2025

ዶቃ









ይህ “ዶቃ “የተሰኘው አማርኛ ፊልም የፓን አፍሪካን የፊልም ፌስቲቫል (Best Feature Film) ዘርፍ እና የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን አሸናፊ መሆን የቻለ ነው ተብሏል::

ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ፊልሙን ለማዘጋጀት ሦስት አመት እንደወሰደባት እና ጥሩ ነገር ለተመልካች አቅርበናል ብላ እንደምታምን ገልጻለች።

በፊልሙ የሃገራችን እንቁ ባለሙያዎች እንደ ቅድስት ይልማ፣ቤዛ ሃይሉ ፣ ማህደር አሰፋ እና ሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች እንደ ተሳተፉበት ታውቋል።

አቶ በሱፍቃድ ተመልካቾች ፊልሙን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት ይቻላል ያሉ ሲሆን፣ ለመመልከት መመዝገብ እና ከፍያ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል።

አቶ በሱፍቃድ ክፍያው ሁሉን ያገናዘበ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ውስጥ 100 ብር፣ለውጭ ደግሞ 5 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቴሌ ቲቪ ከፍያን ለመፈፀም ለሃገር ውስጥ ቴሌብርን ፣ ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና አሜሪካን ኤከስፕረስን በመጠቀም መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል።

ኢግልላየን ፤ቴሌ ቲቪን ጨምሮ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ከመንግስት ተቋማት ፣ ከባንኮች እና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት በማበልጸግ ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

የኢግልይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፍቃድ ፤ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ሰኔ 27 /2016 ዓ.ም “6 ሰዓት ከለሊቱ” እና “ትዝታ” የተሰኙ ሁለት የአማርኛ ፊልሞችን ይዞ መመረቁን አስታውስዋል::







ማክሰኞ 31 ዲሴምበር 2024

ክትፎ


ክትፎ - የኢትዮጵያ ባህላዊ እና ጣፋ ጭ ምግብ


ክትፎ የኢትዮጵያ ባህላዊ እና በጣም ተወዳጅ ምግብ ሲሆን በዋናነት በደቡብ ኢትዮጵያ ይዘጋጃል። ከበሬ፣ በግ ወይም ፍየል ሥጋ የሚዘጋጅ ሲሆን በርበሬ፣ ቅመሞች እና ቅቤ በመጨመር በልዩ ዘዴ ይዘጋጃል።

ጥሬ ሥጋ፡- ክትፎ በተለምዶ የሚሠራው በጥሬ ሥጋ ነው፣ ብዙ ጊዜ የበሬ ሥጋ ነው። የበሬ ሥጋ ምርጫ አስፈላጊ ነው። እና ጥሬው ስለሚበላው ከፍተኛ ጥራት ያለው እና ትኩስ መሆን አለበት።

ቅመም፡- የኢትዮጵያ ምግብ በድምቀት እና ጥሩ መዓዛ ባላቸው ቅመማ ቅመሞች ይታወቃል። ክትፎን በተመለከተ እንደ ሚጥሚጣ፣ ቀረፋ፣ ቅርንፉድ እና ጨው ያሉ ቅመሞች በብዛት ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እፅዋት፡ ነጭ ሽንኩርት እና ዝንጅብል በብዛት በክትፎ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሲሆኑ ጥልቀት እና ጥሩ መዓዛ ያላቸውን ምግቦች ወደ ምግቡ ውስጥ ይጨምራሉ። ሽንኩርት ለተጨማሪ ጣዕም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል.

አዘገጃጀት

የተፈጨ ስጋ፡ ስጋው በጥሩ ሁኔታ የተፈጨ ወይም የተፈጨ ሲሆን ይህም ከታርታር ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሸካራነት ይፈጥራል። ጥሩው ማይኒንግ በወጥኑ ውስጥ ወጥነት ያለው እና ለስላሳ ሸካራነት ያረጋግጣል።

ማጣፈጫ፡- የተፈጨው ስጋ በቅመማ ቅመም እና ቅጠላ ቅይጥ ይቀመማል። ይህ እርምጃ ክትፎን የሚለይ ልዩ እና ጠንካራ ጣዕም ስለሚሰጥ ወሳኝ ነው።

ስታይል ማገልገል፡ ክትፎ ብዙውን ጊዜ የሚቀርበው ከኢንጄራ ጋር ነው፣ የዳቦውን ጣእም የሚያሟላ። የተቀመመ ስጋ ከትንሽ ጣፋጭ ከሆነው ኢንጄራ ጋር መቀላቀል አስደሳች የምግብ አሰራርን ይፈጥራል።




ዳጉ

ዳጉ ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡  ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡...