ረቡዕ 15 ጃንዋሪ 2025

ዳጉ

ዳጉ

ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡ ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ዳጉ ማለት በግርድፉ በአማርኛው ዜና ወይም በእንግሊዝኛ news/እንደ ማለት ነው፡፡ ዳጉ በተለያዩ የእድሜ ክልል የሚገኙ የተለያየጾታ ያላቸው አፋሮች በባህላዊው በታወቀ ስነ-ስረአት መሰረት አድርጎ የሚደረግ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡

 ዳጉ ማለት አንድን መረጃ ማዳመጥ መመልከት ብቻ ሳይሆን እንደሰማውና እንደአየው አድርጎ ለሌሎች ሲያስተላልፍ ባህላዊ ሀላፊነት /ግዴታ ጭምር የሚያቅፍ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

ዳጉ በዘመኑ ቴክኖሎጂ እይታ ከተመለከትነው ዳጉ ገመድ አልባ ፈጣን የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ምንም አይነት ቴክኖሎጂን ሳይጠቀሙ መረጃን በአጭር ጊዜ ወደ ብዙ ቦታ ለብዙ ሰዎች ደርሶ ተግባራዊ ምላሽ የሚደረግበት ባህላዊ

ዘመናዊ መረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ስለሆነም ካንድ ቦታ የተገኘዉ መረጃ በፍጥነት ፣ በጥራት - ሳይዛባ በቶሎ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

ዳጉ መጥፎውን ና ጥሩውን ማህበረሰቡ የሚለይበት ስርአት ነው፡፡ ዳጉ ልክ እንደ ምግብና ውሀ ነው፡፡ አፋሮች ሁሌ ይንቀሳቀሳሉ ትንሽም ብትሆን መረጃ እንድታመልጣቸው አይሹም፡፡ በጠቅላላ ዳጉ ማለት ስለ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ከአንድ ወደ ሌላ የሚተላለፍ መረጃ ነው፡፡ 



ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ዳጉ

ዳጉ ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡  ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡...