ረቡዕ 15 ጃንዋሪ 2025

ዳጉ

ዳጉ

ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡ ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ዳጉ ማለት በግርድፉ በአማርኛው ዜና ወይም በእንግሊዝኛ news/እንደ ማለት ነው፡፡ ዳጉ በተለያዩ የእድሜ ክልል የሚገኙ የተለያየጾታ ያላቸው አፋሮች በባህላዊው በታወቀ ስነ-ስረአት መሰረት አድርጎ የሚደረግ የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡

 ዳጉ ማለት አንድን መረጃ ማዳመጥ መመልከት ብቻ ሳይሆን እንደሰማውና እንደአየው አድርጎ ለሌሎች ሲያስተላልፍ ባህላዊ ሀላፊነት /ግዴታ ጭምር የሚያቅፍ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

ዳጉ በዘመኑ ቴክኖሎጂ እይታ ከተመለከትነው ዳጉ ገመድ አልባ ፈጣን የመረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ምንም አይነት ቴክኖሎጂን ሳይጠቀሙ መረጃን በአጭር ጊዜ ወደ ብዙ ቦታ ለብዙ ሰዎች ደርሶ ተግባራዊ ምላሽ የሚደረግበት ባህላዊ

ዘመናዊ መረጃ መለዋወጫ ዘዴ ነው፡፡ ስለሆነም ካንድ ቦታ የተገኘዉ መረጃ በፍጥነት ፣ በጥራት - ሳይዛባ በቶሎ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

ዳጉ መጥፎውን ና ጥሩውን ማህበረሰቡ የሚለይበት ስርአት ነው፡፡ ዳጉ ልክ እንደ ምግብና ውሀ ነው፡፡ አፋሮች ሁሌ ይንቀሳቀሳሉ ትንሽም ብትሆን መረጃ እንድታመልጣቸው አይሹም፡፡ በጠቅላላ ዳጉ ማለት ስለ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ከአንድ ወደ ሌላ የሚተላለፍ መረጃ ነው፡፡ 



እሑድ 12 ጃንዋሪ 2025

ዳማ ከሴ

 ዳማ ከሴ 

በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን እንደ ከሴ (ስ. ጥሩ ሽታ ያለው የቁጥቋጦ አይነት። ዕቃ ማጠኛ ወይም ኮሰረት  ያለ ለመድኅኒትነት የሚጠቀሙበት ነው።

ይሄ ዕጽ በሺ ስድስት መቶ እስከ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሜትር ከፍታ ባሉ ሥፍራዎች የሚበቅል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ለመድኅኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሐ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።

የዳማ ከሴ ተጨማሪ ጥቅሞችለ

ጉንፋን፣ ለራስ ምታትና ለውሻ ልክፍት (በተለምዶ - ያድን አያድን አይታወቅም) ይጠቀማል።



ማክሰኞ 7 ጃንዋሪ 2025

ራያ

  ራያ

 በደቡብ ትግራይ እና በሰሜን ወሎ የሚገኝ ህዝብ  እና አካባቢ ነው። ይህ ህዝብ በትግራይ እና በወሎ ካሉ ደማቅ ባህሎች ባለ ቤት ስርዓት እና ወግ፡ ማለትም እንደ አነጋገር፡ አለባበስ፡ የሰርግ ፡ የለቅሶ ስነስርዐት ያለው ኩሩ እና ጀግና ህዝብ ነው። የራያ ህዝብ ከሚደነቅበትና ከሚያስደስት ባህሉ ሁሉም የእምነት ተከታዮች በተለይም ሙስሊም  ክርስቲያን  ሳይል በመቻቻል በህብረት በአንድ ላይ ተከባበሮ የሚኖር ህዝብ ሲሆን የአለባበስ ባህሉ ሌላው የሚደነቅለት አና ባህላዊ ጭፈራው ሲያዩት የሚያስግርም አና የሚያስድስት ነው። ከባህላዊ ጭፈራዎቹ እንደ "ጉማየ" "መጋልዋ" ፡ ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝቡ የሚኖርበት አከባቢ እንደሚከተለው ይዋሰናል። በሰሜን ወጀራትና እንደርታ፣ በደቡብ የጁ (ጉባ ላፍቶ) እና ሃብሩ፣ በምስራቅ ዓፋር፣ በምዕራብ ደግሞ ግዳን እና ዋግኽምራ ያዋሱኑታል።




ዓርብ 3 ጃንዋሪ 2025

ዶቃ









ይህ “ዶቃ “የተሰኘው አማርኛ ፊልም የፓን አፍሪካን የፊልም ፌስቲቫል (Best Feature Film) ዘርፍ እና የለዛ ሽልማት የአመቱ ምርጥ ፊልም በመሆን አሸናፊ መሆን የቻለ ነው ተብሏል::

ተዋናይት እና ፕሮዲውሰር ማህደር አሰፋ ፊልሙን ለማዘጋጀት ሦስት አመት እንደወሰደባት እና ጥሩ ነገር ለተመልካች አቅርበናል ብላ እንደምታምን ገልጻለች።

በፊልሙ የሃገራችን እንቁ ባለሙያዎች እንደ ቅድስት ይልማ፣ቤዛ ሃይሉ ፣ ማህደር አሰፋ እና ሌሎችም የፊልም ባለሙያዎች እንደ ተሳተፉበት ታውቋል።

አቶ በሱፍቃድ ተመልካቾች ፊልሙን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ከዛሬ ነሃሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት ይቻላል ያሉ ሲሆን፣ ለመመልከት መመዝገብ እና ከፍያ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አንስተዋል።

አቶ በሱፍቃድ ክፍያው ሁሉን ያገናዘበ መሆኑን ገልጸው ለሀገር ውስጥ 100 ብር፣ለውጭ ደግሞ 5 ዶላር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቴሌ ቲቪ ከፍያን ለመፈፀም ለሃገር ውስጥ ቴሌብርን ፣ ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ ተመልካቾች ደግሞ ቪዛ፣ ማስተርካርድ እና አሜሪካን ኤከስፕረስን በመጠቀም መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል።

ኢግልላየን ፤ቴሌ ቲቪን ጨምሮ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ከመንግስት ተቋማት ፣ ከባንኮች እና ከአለማቀፍ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት በማበልጸግ ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ ሰምተናል፡፡

የኢግልይን መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፍቃድ ፤ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን በቴሌ ቲቪ መተግበሪያ ሰኔ 27 /2016 ዓ.ም “6 ሰዓት ከለሊቱ” እና “ትዝታ” የተሰኙ ሁለት የአማርኛ ፊልሞችን ይዞ መመረቁን አስታውስዋል::







ዳጉ

ዳጉ ዳጉ በአፋር ህዝብ ዘንድ ለዘመናት አብሮ ያለ ከአፋር ማንነት ፈጽሞ ሊለይ የማይችል ትልቅ ባህላዊ የመገናኛ ዘዴ ነው፡፡  ዳጉ የተለያዩ ጥናቶች የተለያዩ ትርጓሜ የሰጡት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡...